loading
ኬንያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የጣለችው የሰዓት እላፊ ገደብ ለተጨማሪ አንድ ወር አራዘመች::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 21፣ 2012 ኬንያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የጣለችው የሰዓት እላፊ ገደብ ለተጨማሪ አንድ ወር አራዘመች::የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በመግለጫቸው እንዳሉት በዚህ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የምት ከለቦችና መጠጥ ቤቶች ዝግ እንደሆኑ ይቆያሉ፡፡ በሰርግ፣ በቀብር ስነ ስርዓቶችና በሌሎችም ሁነቶች ላይ የሚገኙ ሰዎች ግን ቁጥራቸው ካልበዛና እርቀታቸውን እስከጠበቁ ድረስ አይከለከሉም ነው የተባለው፡፡ ኬንያታ ምንም እንኳ በሀገራችን የቫይረሱ የስርጭት መጠን ከነበረበት 13 በመቶ ወደ 8 በመቶ ዝቅ ያለ ቢሆንም ችግሩ አሁንም አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በናይሮቢ እና ሞምባሳ አካባቢዎች በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳይም በገጠራማው የሀገሪቱ ክፍሎች መስፋፋት እያሳየ ነው ተብሏል፡፡ ኮቪድ-19 የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እየጎዳው ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ በሆርቲካልቸር ዘርፍ የተገኘው የተሻለ ገቢ አካከሶልናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በኬንያ እስካሁን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ33 ሺህ በላይ የደረሰ ሲሆን ከ560 በላይ ዜጎቿ በበሽታው ሳቢያ ህይዎታቸው አልፏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *