loading
ኬንያ እና ሶማሊያ በባህር ድንበር ጉዳይ ተፋጠዋል፡፡

ኬንያ እና ሶማሊያ በድንበር ጉዳይ ተፋጠዋል፡፡

ሁለቱ የምስራቅ አፍሪካ ጉረቤታሞች ከ100 ሽህ ስኩየር ኪሎ ሜትር በላይ በሚዋሰኑበት በህንድ ወቅያኖስ ነው አዲስ ውዝግብ ውስጥ የገቡት፡፡

ኬንያ እና ሶማሊያ ቀደም ሲል ያነሱት የይገባኛል ጥያቄ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት እየታየ ቢሆንም  እስካሁን ለየትኛውም ወገን አልተወሰነም፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው ኬንያ በሶማሊያ ያሉትን አምባሳደሯን ወደ ናይሮቢ ጠርታለች፤ የሶማሊያን አምሳደርም ወደ ሀገርዎ ሄደው ከመንግስትዎ ጋር ይምከሩ ብላቸዋለች፡፡

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እዚህ ውሳኔ ላይ የደረስነው ሶማሊያ በግዴለሽነት እና በማን አለብኝነት በአካባቢው የነዳጅ ፍለጋ ስፍራ ያወጣችው የተናጠል ጨረታ ነው ብሏል፡፡

ሶማሊያ በበኩሏ የተካሄደ ጨረታ የለም ኬንያ ከየት እንዳመጣችው አላውቅም ማስረጃ ካላት ታቅርብ ብላለች፡፡

ኬንያ ግን ሞቃዲሾ በፈረንጆቹ የካቲት ሰባት ለንደን ላይ ጨረታውን አካሂዳለች ፤ይህንም ጉዳይ ከቀኑ አስቀድመን ለሶማሊያ መንግስት አንስተንለት ነበር በማለት እርምጃውን ያለ ምክንያት እንዳልወሰደች ተናግራለች፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *