ኬንያ የብሉ ኢኮኖሚ ኮንፈረንስ እያስተናገደች ነው
አርትስ 17/03/2011
ናይሮቢ ለዘመናት መልስ ያላገኘውን እና ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀጣይነት ያለው ልማትና የ2030 አጀንዳ ጋር በተገናኘ መሪ ሀሳብ ኮንፈረንሱን እያካሄደች ነው፡፡
ለሶስት ቀናት የሚቆየው ይህ ኮንፈረንስ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ያለው ሲሆን ከ20 በላይ የዓለማችን መሪዎች እየተሳተፉበት ነው፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ኮንፈረንሱ ብሉ ኢኮኖሚና የ2030 አጀንዳ ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚካሄደው፡፡
ጉባኤው በውሃ ላይ የተመሠረተ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን ለማሳደግ እዲሁም የውሀ አካላትን ስነ-ምህዳርና ብዝሃነት ለመጠበቅ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
ኬኒያ ጉባኤውን ያዘጋጀው ከጃፓንና ከካናዳ ጋር በመተባበር ሲሆን ከ184 ሀገራት የተውጣጡ ከ17 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችም ይገኙበታል ነው የተባለው፡፡
ውሀ በዓለማችን 24 ትሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት እንዳለው በጥናት ያረጋገጡት የዘርፉ ባለሞያወች ይናገራሉ፡፡
የዚህ ስብሰባ ዋነኛ ዓላማም ከዓሳ ሀብት፣ ከውሀ ትራንስፖርት፣ ከቱሪዝምና ሌሎች ዘርፎች በየዓመቱ ቢያንስ 2.5 ትሪሊዮን ዶላር ማግኘት እንዲቻል ምክረ ሀሳብ ማቅረብ ነው