loading
ውድ የኢትዮጵያ ልጆች አድሏዊውን ዓለም እርቃኑን አስቀርታችሁታል-አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 መንግስት ያቀረበውን ወደ ሀገር ቤት ጥሪ ተቀብለው ለገቡ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የአቀባበል መርሃግብር ተካሄደ፡፡በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለእንግዶቹ እንኳን ወደ እናት ሀገራችሁ በሰላም መጣችሁ የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
አቶ ደመቀ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ኖ ሞር በሚለው ንቅናቄ ይህን አድሏዊ ዓለም እርቃኑን አስቀርታችሁታልና ሀገርና ወገን ኮርቶባችኋል ብለዋል፡፡


የኢትዮጵያ ዳስፖራ ኤጄንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኮሚቴው ሴክሬተሪያት ዶክተር መሀመድ ኢድሪስ በበኩላቸው “መድረኩ በአካል ተለያይተው የነበሩ ነገር ግን ልቦናቸው የተገናኙ የአንድ ሀገር ልጆች የተገናኙበት መድረክ ነው ብለዋል፡፡ በስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችም ተገኝተዋል፡፡


ከንቲባዋ ባደረጉት ንግግር ጉዙ ወደ ሃገር የሚለውን የፍቅር ጥሪ ተቀብላችሁ በመምጣታችሁ ነፃነትን ከነድንበሩ፣ ማሸነፍን ከነክብሩ ገልጻችኋልና ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል፡፡ ጥሪውን ተቀብለው በተለያዩ ቀናት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዳያስፖራዎች የተለያዩ መርሃግብሮችን የሚታደሙ ሲሆን እስከ ጥምቀት በዓል ድረስ ያሉ ታላላቅ አገራዊ ሁነቶችንም እንዲሳተፉ እቅድ ተይዟል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *