loading
ዓለም ባንክ ለታዳጊ ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባት ግዢ የሚውል 12 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 ዓለም ባንክ ለታዳጊ ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባት ግዢ የሚውል 12 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ::የባንኩ ዳሬክተሮች ቦርድ ይፋ ባደረገው መሰረት ለታዳጊ ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባት ግዢና ለዜጎቻቸው ምርመራና እንክብካቤ የሚውል 12 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አጽድቋል

የገንዘብ ድጋፉ ለአንድ ቢሊዮን ሰዎች ክትባት ማዳረስ የሚያስችል ሲሆን የዓለም ባንክ እስከ ፈረንጆቹ 2021 ድረስ ታዳጊ ሀገራት ወረርሽኙን እንዲከላከሉ ካስቀመጠው 160 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እቅድ አንዱ ነው ተብሏልየዓለም ባንክ ለታዳጊ ሀገራት የያዘው የገንዘብ ድጋፍ ለ111 ሀገራት ለአስቸኳይ ጊዜ ፕሮግራም እንዲውል ይከፋፈላል ሲልም ተናግሯል

አስተማማኝና ውጤታማ ክትባት ማቅረብና የአቅርቦት ስርዓቱን ማጠናከር ወረርሽኙን ለመዋጋት ወሳኝ መሆኑን የተናገረው ባንኩ ታዳጊ ሀገራት ወረርሽኙ ከሚያስከትልባቸው የኢኮኖሚ ጫና በአፋጣኝ እንዲያገግሙ ማስቻል ዋነኛ ዓላማው እንደሆነ መናገሩን ሽኑዋ ዘግቧል::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *