ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፕዚዳንት ሎረን ባግቦን የይግባኝ ክርክር መስማት ጀመረ::
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2012 ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፕዚዳንት ሎረን ባግቦን የይግባኝ ክርክር መስማት ጀመረ::ፍርድ ቤቱ የቀድሞውን ኮትዲቯር ፕሬዚዳንት ሎረን ባግቦ ከቀረበባቸው ክስ ነፃ ናቸው ማለቱን ተከትሎ አቃቤ ህግ ይግባኝ በመጠየቁ ነው ዳግም ጉዳያቸው መታየት የጀመረው፡፡
የባግቦን የክስ ሂደት የያዙት ጋምቢያዊቷ አቃቤ ህግ ፋቱ ቦም ቤንሶዳ ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ህጋዊም ስነስርዓታዊም ስህተቶችን ሰርቷል ብለዋል፡፡ባግቦ በአለም አቀፉ ፍርድ ቤት የተዳኙ የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ሲሆኑ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር 2010 እና 11 ከምርጫ በኋላ በተፈጠረ አለመረጋጋት ለጠፋው የሰዎች ህይዎት እጃቸው አለበት ተብለው ነው የተከሰሱት፡፡አልጀዚራ እንደዘገበው በወቅቱ የምርጫውን ውጤት ተከትሎ በተከሰተው ብጥብጥ ከ3 ሺህ በላይ
ዜጎች ህይዎታቸው አልፏል፡፡ ፕሬዚዳንት ባግቦ አለም አቀፉ ፍርድ ቤት ነጻ ቢለቃቸውም የኮትዲቯር ፍርድ ቤት ከሀገሪቱ ማእከላዊ ባንክ ገንዘብ አጭበርብረዋል በሚል የ20 ዓመት እስር ፈርዶባቸዋል፡፡ባግቦና በሳቸው የስልጣን ዘመን የወጣቶች ሚኒስትር የነበሩት ቻርለስ ብሌ ጎዴ የችሎት ውሎ ቦኮሮናቫይረስ ምክንያት በከፊል በቪዲዮ ኮንፈረንስ ነው የሚካሄደው ተብሏል፡፡