loading
ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ተቋም በስደት ላይ ያሉ ሰዎች የኮሮቫይረስ ክትባት እንዲያገኙ ጥሪ አቀረበ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2013 ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ተቋም በስደት ላይ ያሉ ሰዎች የኮሮቫይረስ ክትባት እንዲያገኙ ጥሪ አቀረበ:: ተቋሙ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ባቀረበው ጥያቄ ህብረቱ ፍልሰተኞቹ እንደሌላው ዜጋ ሁሉ እኩል ተደራሽነት ያለው የክትባት አገልግሎት ሊያገኙ ይገባል ብሏል፡፡

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አንቶኒዮ ቪቶሪኖ የአንዱ ጤና መሆን ለሌላው ዋስትና ስለሆነ የስደተኞቹን ደህንነት መጠበቅ ጥቅሙ ለነሱ ብቻ ሳይሆን ላስጠለሏቸው ሀገራትም ጭምር መሆኑ መታወቅ አለበት ብለዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የአውሮፓ ፓርላማና ጀርመን በመተባበር በስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ዙሪያ
የሚመክር የቪዲዮ ኮንፈረንስ አዘጋጅተው ሰፋ ያለ ውይየት ተደርጓል፡፡

ቪቶሪኖ በውይይቱ ወቅት ሀገራት ስለክትባት ሲያስቡ በግዛታቸው ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን ታሳቢ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡
በስደት የሚኖሩ ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ልዩ ትኩረት ሊደረግላቸው እንደሚገባም በውይይቱ ወቅት ተነስቷል ነው የተባለው፡፡ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ተቋም አይ ኦ ኤም በአውሮፓ ሀገራት የጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝም ጠይቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *