loading
ዛምቢያ የነፃነት አባቷን በሞት ተነጠቀች::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11፣ 2013 በዛምቢያዊያን ዘንድ የነፃነት አባት በመባል የሚታወቁት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኬኔት ካውንዳ በ97 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ካውንዳ ከቀናት በፊት ሉሳካ ወደሚገኘው ወታደራዊ ሆስፒታል ገብተው ህክምናቸውን ቢከታተሉም ሀኪሞቻቸው ህይዎታቸውን ማትረፍ አልተቻላቸውም፡፡

የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በሰጡት መግለጫ በሽታቸው ከሳንባ ምች ጋር የተገናኘ እንደሆነ ይፋ አድርገዋል፡፡

ረዳታቸው ሮድሪክ ንጎሎ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ካውንዳ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተው ነው የሞቱት የሚለውን ወሬ አስተባብለዋል፡፡

በግጭት አልባ የአመፅ እንቅስቃሴያቸው “አፍሪካዊው ጋንዲ” የሚል ቅጽል ስም የተሰጣቸው ካውንዳ፤ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር የነበረችውን ሰሜን ሮዴሽያ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በወርኃ ጥቅምት 1964 ወደ ደም አልባ ነፃነቷ እንድታመራ አድርገዋል፡፡

በአንፃሩ ሶሻሊስቱ ካውንዳ ዛምቢያን ለ27 ዓመታት በአንድ ፓርቲ አገዛዝ ስር የመሩ ሲሆን ሀገሪቱ በመልካም አስተዳደር እጦት ወደ ከባድ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ እንድታመራ ምክንያት መሆናቸወም ይነገራል፡፡

በዚህም የተቀሰቀሰውን አመፅ ተከትሎ እ.ኤ.አ. በ1991 በሀገሪቱ ነፃ ምርጫ እንዲደረግ ተስማምተው ተሸናፊ ሆነዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *