loading
ዛሬ ምሽት ተጠባቂ የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ይደረጋሉ

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች፤ ዛሬ እና ነገ ምሽት ይከናወናሉ፡፡ ዛሬ ምሽት የሚከናወኑት ጨዋታዎች 4፡ 00 ላይ ይጀመራሉ፡፡

ባለፈው ሳምንት ኦልድ ትራፎርድ ላይ የ1 ለ 0 ድል ያስመዘገበው የስፔኑ ባርሴሎና ካምፕ ኑ ላይ ማንችስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡

ቀያይ ሰይጣኖቹ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ለማለፍ ሜዳቼው ላይ የገጠማቸውን ሽንፈት መቀልበስ ይኖርባቼዋል፡፡

በመጀመሪያው ጨዋታ በክሪስ ሰሞሊንግ ፊቱ ላይ ጉዳት ደርሶበት የነበረው ሊዮኔል ሜሲ በምሽቱ ግጥሚያ የሚያሰጋው የለም ተብሏል፡፡

በሶልሻዬር ቡድን በኩል አሌክሲስ ሳንቼዝ እና ኒማኒያ ማቲች ከጉዳት መልስ ለጨዋታ ዝግጁ ናቸው ተብሏል፡፡

በ22 ተጫዋቾች ስብስብ ውስጥ ማቲዎ ዳርሚያን የተካተተ ሲሆን አንደር ሄሬራ እና ኢሪክ ቤይሊ በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ውጭ ናቸው፡፡

ከዚህ ቀደም ባርሴሎና በሜዳው ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ባደረገው ጨዋታ ሽንፈት ገጥሞት አያውቅም፤ በሁለቱ ድል ሲቀናው በቀሪዎቹ ደግሞ አቻ ተለያይቷል፡፡

ባርሳ ወደ ግማሽ ፍፃሜው የሚያልፍ ከሆነ ከሊቨርፑል እና ፖርቶ አሸናፊ ጋር ይገናኛል፡፡

የኔዘርላንድሱ አያክስ አምስተርዳም ወደ ጣሊያን አምርቶ በአሊያንዝ ስታዲየም ዩቬንቱስን ይገጥማል፡፡

አምስተርዳም ላይ በተካሄደው የመጀመሪያ ጨዋታ ዩቬ ተፈትኖ በአቻ ውጤት መለያየቱ ይታወሳል፡፡

በቻምፒዮንስ ሊጉ ስም ያለው ፖርቱጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በምሽቱ አሮጊቷ አብዝታ ትጠብቅበታለች፡፡

የኔዘርላድሱ ቡድን ተጫዋቾች ሜዳቸው ላይ ያሳዩትን የጨዋታ ብልጫ በጣሊያን ምድር ሊደግሙት እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡

የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ ከማንችስተር ሲቲ እና ቶተንሃም ሆተስፐር ቀጣዩ ዙር ላይ ይገናኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *