የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያ ፈተናዎቿን በድል ተሻግራ ችግሯን በራሷ ፈታ ወደፊት የቀጠለች መሆኑን የምናሳይበት ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ::
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያ ፈተናዎቿን በድል ተሻግራ ችግሯን በራሷ ፈታ ወደፊት የቀጠለች
መሆኑን የምናሳይበት ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ::
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት
መግለጫ በአዲስ አበባ የሚካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያ ፈተናዎቿን
በድል ተሻግራ በቁርጥ ቀን ልጆቿ ችግሯን በራሷ ፈታ ወደፊት የቀጠለች መሆኑን የምናሳይበት ነው
ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ በመግለጫቸው፥ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ ብዙ ቅስቀሳ
እንደነበር አንስተው፥ ሆኖም አባል ሀገራቱ ለህብረቱ ህግና መርህ ተገዢ በመሆን ጉባኤው በአካል
በአዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰናቸውን ነው ያስታወሱት።
በዚህም ውሳኔያቸው ለኢትዮጵያ ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል ያሉት ሚኒስትሩ፥ ይህም ተግባራቸው
የሚያስመሰግናቸው ነው ብለዋል።