loading
የሊቢያ ተፋላሚ ኃይሎች ስምምነት

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣ 2013  የሊቢያ ተፋላሚ ኃይሎች ቁልፍ የመንግስት ተቋማትን የሚመሩ እጩዎችን ለመምረጥ ተስማሙ ::የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ሞሮኮ ላይ ባደረጉት አዲስ ውይይት የእጩዎቹ የምልመላ ሂደት ከማክሰኞ ጀምሮ እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡ ተፋላሚ ሃይሎቹ የደረሱበት ስምምነት በሀገሪቱ ለአስር ዓመታት የተካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነት እንዲያበቃ ለማድረግ ሁነኛ መፍትሄ መሆኑ ነው የተመገረለት፡፡

ሂደቱ እስከመጭው ፌብሩዋሪ 2 ቀን ድረስ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከፍተት ያለባቸው ስትራቴጂያዊ ቦታዎንች በፍጥነት ለመሙላት ያለመ ነው ተብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በሚቀጥለው ሳምንት በጄኔቫ ከሚመረጠው አስፈፃሚው አካል ጋር በትብብር ለመስራት መዘጋጀታቸውን ተወካዮቹ በጋራ በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል፡፡

ሞሮካ ላይ የተካሄደው ውይይት መሰረቱን ትፖሊ ያደረገውን ምክር ቤትና ነፍጥ አንግበው ውጊያ የጀመሩትን የምስራቃዊ ሊቢያ ተቃዋሚዎችን አንድ አድርጓል ነው የተባለው፡፡ ሁለቱ ወገኖች ባለፈው ጥቅምት ወር የተፈራረሙት የተኩስ አቁም ስምምት በጄኔራል ከሊፋ ሀፍታር ጦር እንዳይጣስ ስጋት ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ከሞላ ጎደል መከበሩ ነው የተነገረው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *