loading
የሱዳን ናሽናል ኡማ ፓርቲ የአረብ እስራኤል ዲፕሎማሲ ሰላምን ለማምጣት አስተዋፅዖ የለውም ሲል አጣጠለ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 የሱዳን ናሽናል ኡማ ፓርቲ የአረብ እስራኤል ዲፕሎማሲ ሰላምን ለማምጣት አስተዋፅዖ የለውም ሲል አጣጠለ:: የፓርቲው መሪ የቀድሞው የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አልመሃዲ እስራኤል ከአረቡ ዓለም ጋር የጀመረችውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት መደገፍ እጅ እንደመስጠት ይቆጠራል ብለዋል፡፡ ኖርማላይዜሽን በሚል አዲስ ታክቲክ እስራኤል የጀመረችው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ሰላምን ከማምጣት ይልቅ ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ መስፈፀሚያ ነው ሲሉም አልማሃዲ ተናግረዋል፡፡

እንቅስቃሴው ኢራንን ለጦርነት ማመቻቸት እና የጠቅላይ ሚስትር ቤናሚን ኔታኒያሁና የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ስልጣን ለማራዘም ያለመ ይመስላል በማለትም አብራርተዋል፡፡በሱዳን የሉአላዊ ምክር ቤት መሪ አብደልፈታህ አልቡራሃን የተመራው ልኡካን ባለፈው ሳምንት ወደ አቡዳቢ በመጓዝ በጉዳዩ ዙሪያ ቢመክርም ስምምነት ላይ እንዳተልደረሰ ሱዳን ትሪበዩን ዘግቧል፡፡ሱዳን የአረብ እስራኤንል የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንድትደግፍ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ይልቅ የካውንሱሉ መሪ አብደልፈታህ አልቡራሀን የበለጠ ፍላጎት እንዳላቸው ዘገባው አክሎ አትቷል፡፡ ሱዳን በአሜሪካ አደራዳሪነት የሚካሄደውን የአረብ እስራኤል ግንኙነት የምትደግፈው በዋሽንግተን ከተመዘገበችበት የሽብር መዝገብ ስሟን ለማስሰረዝ እንዲረዳት በማሰብ መሆኑ ይነገራል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *