loading
የሳኡዲ አረቢያ መንግሰት የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ የረጂም ጊዜ ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩ 1400 ኢትዮጵያውያን በምህረት ለቀቀ፡፡

የሳኡዲ አረቢያ መንግሰት የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ የረጂም ጊዜ ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩ 1400 ኢትዮጵያውያን በምህረት ለቀቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳምንታዊዉ  መግለጫዉ እንዳስታወቀዉ ምህረት ከተደረገላቸዉ ታራሚዎች በተጨማሪ አሁን በእስር ላይ የሚገኙ ቀሪ ታራሚዎች የእስር ጊዜያቸው በ75 በመቶ እንደሚቀንስላቸው የአገሪቱ ባለስልጣናት ማሳወቃቸውን ተነግሯል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው  በወቅታዊ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ዙሪያ 67ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ሚያዝያ 29 ቀን 2011 ዓም በጁባ መካሄዱን ያስታወሱ ሲሆን፤ በዚህም ተደራደራ ወገኖች ባለፈው ወር በአዲስ አበባ ባደረጉት ውይይት ቀሪ ስራዎችን በቀጣዩ ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የጊዜ ገደብና አመላካች ነጥቦችን በግልጽ በማስቀመጥ ለመፈጸም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተቋሙ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ ወዲህ የመጀመሪያ የውጭ ጉብኝታቸውን ሚያዝያ 27 እና 28 ቀን 2011 ዓም በሱዳን ካርቱም ማድረጋቸውን ተናግረዉ፤በጉበኝታቸውም ከሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር፣ ከሱዳን ”የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች” ተወካዮች ጋር እንዲሁም በሱዳን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲመሰረት ከሚሰሩ ታዋቂ አካላት ጋር የተናጥል ውይይት አድርገዋል ብለዋል ።

በዚህም ኢትዮጵያ በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ሳትገባ የሱዳንን ሉዓላዊነት በማክበር የሱዳንን ህዝብ ፍላጎት መሰረት አድርጋ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ በሱዳን በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማቆያና ማገገሚያ ማዕከል በመጎብኘት በማዕከሉ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ጋር ውይይት አድርገዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያና አውሮፓ ህብረት ቢዝነስ ፎረም እ.ኤ.አ ከሜይ 14-15 ቀን 2019 በቤልጂዬም/ብራሰልስ እንደሚካሄድና በመድረኩም የኢትዮጵያ ለአውሮፓ ባለሃብቶች ያላት ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮችም እንደሚዳሰሱበት አስታውቀዋል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *