loading
የስድስት ኪሎ አንበሳ ጊቢ በቅርቡ ስራ ይጀምራል ተባለ

የስድስት ኪሎ አንበሳ ጊቢ በቅርቡ ስራ ይጀምራል ተባለ

አርትስ 14/03/2011

እድሳቱ የተጓተተውና ሁለት አመታትን የፈጀው የአዲስ ዙ ፓርክ ፤በውስጡ የንግድ ሱቆችን ፥ የመመገቢያ ካፍቴሪያ፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የአዕዋፍ ዝርያዎችን ማሳያ ወስከምት(ኬጅ) ጨምሮ  ሁሉም አገልግሎቶች ስራ ይጀምራሉ፡፡
ከመስከረም 21, 2009 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት መስጠት አቁሞ የነበረው  የስድስት ኪሎ አንበሳ ጊቢ  በውስጡ አስር አናብስት ፤6 ሴት እና 4 ወንድ፤ዝንጀሮዎች፣ ጦጣዎች፣ አምባራይሌ እና ሌሎች የዱር እንስሳትም አሉት ተብሏል፡፡

የከንቲባ ጽ/ቤት እንዳስታወቀዉ  የፓርኩን አሰራር በመቀየር እና የእንስሶቹን አመጋገብ በማዘመን ተከስቶ የነበረውን የእንስሳት ክብደት መቀነስ፤ የበሽታ ተጋላጭነት መቀረፉን እና የአስተዳደር እና ተያያዥ ችግሮችም ተፈተዋል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *