loading
የሶማሊያው አልሻባብ የኮሮና ቫይረስ ማከሚያ ማዕከልን አቋቁመ::

አዲስ አበባ፣ሰኔ 7፣2012 የሶማሊያው አልሻባብ የኮሮና ቫይረስ ማከሚያ ማዕከልን አቋቁመ:: ሶማሊያ ላይ የመሸገው ፅንፈኛው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን፤ በሀገሪቱ ውስጥ የኮቪድ-19 ሕክምና ማዕከል ማቋቋሙን ገልፆ፤ የዓለም አቀፍ የጤና ባለሥልጣናትን ትንበያ በመጥቀስ በሽታው ከባድ ስጋት እንዳስከተለ ገልጧል ፡፡ ታጣቂ ቡድኑ መልዕክቶችን በሚያስተላልፈበት የአንዳሉስ ራዲዮ ስርጭት አል- ሸባብ የኮሮና ቫይረስ መከላከል እና እንክብካቤ ኮሚቴ በማቋቋም የኮቪድ-19 ማዕከል መገንባቱን አስታውቋል፡፡ ጨምሮም ይህ ማዕከል በሀገሪቱ መዲና ሞቃዲሹ ደቡብ አቅጣጫ 380 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ጂሊብ ከተማ እንዳተቋቋመ አስታውቋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአህጉረ አፍሪካ ሀገራት በአሰቃቂ ሁኔታ እየተሰራጨ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል፡፡የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የምዕራባውያን አስተምህሮ እና መንግስታዊ ስርዓት እንዳያራምዱ እና የራሱን ስርዓተ መንግስት በራሱ እስላማዊ የሸሪዓ ህግጋት አረዳድ ለመምራት ሲታገል ከአስር ዓመት በላይ ተቆጥረዋል፡፡  ቡድኑ ይሄንን ዓላማውን ለማሳካት ሆቴሎችን፣ መገናኛዎችን እና የደህንነት ተቋማትን ጨምሮ በሶማሊያ የተለያዩ ቁልፍ ቦታዎች በወታደራዊ እና ንፁሃን ዜጎች ላይ በማነጣጠር የመሳሪያ እና የቦንብ ጥቃቶችን በተደጋጋሚ ይፈጽማል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *