loading
የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች ማሩዋን ቻማክ ጫማ ሰቅሏል፡፡

በተለያዩ ክለቦች የተጫወተው ሞሮኳዊው ኢንተርናሽናል ማሩዋን ቻማክ ላለፉት

ሁለት ዓመት ከግማሽ ሳይጫወት ከቆየ በኋላ በ35 ዓመቱ በይፋ እግር ኳስ  መጫወት ማቆሙን አስታውቋል፡፡

የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች በዌስት ሃም ዩናይትድ፣ ክሪስታል ፓላስ፣ ካርዲፍ ሲቲ እና የፈረንሳዩ ቦርዶ ተጫውቶ አሳልፏል፡፡

ተጫዋቹ በ2016 የዌልሱን ካርዲፍ ከተሰናበተ በኋላ ያለምንም ክለብ ቆይታ አድርጓል፡፡

ቻማክ ለቤን ስፖርትስ እንዳለው በእውነት ዛሬ ከእግር ኳስ መገለሌን አስታውቃለሁ ሲል ገልጧል፡፡

በፈረንሳይ የተወለደው ቻማክ ስምንት ዓመታትን በቦርዶ በማሳለፍ፤ በ230 የሊጉ ጨዋታዎች ላይ 56 ጎሎችን በማስቆጠር፤ አንድ የሊግ አንድ እና የፈረንሳይ ሊግ ዋጫዎችን ማሳካት ችሏል፡፡

በ2010 ወደ አርሰናል መጥቶ በሶስት የውድድር ዓመት ቆይታው፤ በ40 የፕሪምየር ሊግ ግጥሚያዎች ላይ ተሰልፎ ስምንት ጎሎችን ብቻ አስቆጥሯል፡፡

ቻማክ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ለፈረንሳይ ከ19 ዓመት በታች ቢሰለፍም፤ ዋናውን የብሄራዊ ቡድን አገልግሎት ግን ለሞሮኮ ከ2003 ጀምሮ ሰጥቷል፡፡ ለሀገሩም በ68 ግጥሚያዎች 18 ግቦችን ማበርከት ችሏል፡፡   

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *