loading
የባለቤትነት ካርታ በመከነባቸው ቦታዎች ላይ የተዘጋጁት አዳዲሶቹ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች ሥራ ጀመሩ

የባለቤትነት ካርታ በመከነባቸው ቦታዎች ላይ የተዘጋጁት አዳዲሶቹ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች ሥራ ጀመሩ

አርትስ 01/04/11

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለዓመታት በባለይዞታዎች ባለመልማታቸው ምክንያት የባለቤትነት ካርታ ካመከነባቸው ቦታዎች መካከል፣ በአሥሩ ላይ ያዘጋጃቸው ጊዜያዊ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራዎች ሥራ መጀመሩን አስታዉቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ለተሽከርካሪ ማቆሚያ ከጠየቃቸው 56 ቦታዎች መካከል 20 ቦታዎች የተፈቀዱለት ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ በአሥሩ ላይ የተዘጋጁት የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች ቅዳሜ እለት በይፋ ሥራ ጀምረዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ጊዜያዊና ዘላቂ የተሽከርካሪዎች ማቆሚያዎችን ከመገንባት ባሻገር፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የንግድ ሕንፃዎች ለተሽከርካሪዎች ማቆሚያ የገነቡትን ቦታ ለሌላ ተግባር ያዋሉ መሆኑን ጠቅሶ፣ ቦታውን ለተሽከርካሪዎች ማቆሚያ እንዲያውሉ የአንድ ወር ጊዜ ሰጥቷል፡፡

ሪፖርተር እንደዘገበዉ በአሁኑ ወቅት በከተማው 120 የመንገድ ዳር የክፍያ ተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታዎች አሉ፡፡ እነዚህን ጨምሮ በአዳዲሶቹ ተሽከርካሪ ማቆሚያዎችየሚሠሩት በጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች የተደራጁ ወጣቶች ናቸው ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *