የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና የቀድሞው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ተክለብረሃን ወልደአረጋይ በቁጥጥር ስር ዋሉ
ሰበር ዜና
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና የቀድሞው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ተክለብረሃን ወልደአረጋይ በቁጥጥር ስር ዋሉ
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለፋና እንደገለፀው ተጠርጣሪዎቹ በወጣባቸው የእስር ማዘዣ መሰረት ወደ ሱዳን ለመውጣት ሲሞክሩ ሁመራ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውለው ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ መሆኑ ተገልጿል።
ከተያዙ በ48 ሰዓታት ውስጥ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ሌሎች የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው ትናንት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን በእነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይም ፍርድ ቤቱ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወቃል፡፡