የአልበሽር ጠበቆች ቅሬታ::
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2013 የአልበሽር ጠበቆች ቅሬታ::በአቃቤ ህግ ቅር የተሰኙ የአልበሽር ጠበቆች ችሎት ረግጠው ወጡ:: የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ተከላካይ ጠበቆች አቃቤ ህግ አድሏዊ የሆነ ክርክር አቅርቦብናል ሲሉ ከሰዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከፕሬዚዳንቱ ጠበቆች መካከል የተወሰኑት የዕለቱን ክርክር በመተው ችሎቱን ረግጠው መውጣታቸው ተሰምቷል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው አልበሽር በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ እስከሞት የሚያደርስ ቅጣት ሊተላለፍባቸው ይችላል፡፡
አልበሽር እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1989 የወቅቱን አስተዳደር በመፈንቅለ መንግስት አስወግደው ስልጣን በመያዛቸው ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ ከአጋሮቻቸው ጋር በዳርፉር አደረሱት በተባለው የዘር ማጥፋትና የጦር ወንጀል እስካሁን በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ይፈለጋሉ፡፡ አልበሽር እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2019 በታማኝ ጄኔራሎቻቸው የመፈንቅለ መንግስት ከተደረገባቸው ጊዜ አንስቶ በእስር የሚገኙ ሲሆን በቤታቸው ህገ ወጥ ገንዘቦች ተገኝተውባቸዋል በሚልና በሌሎችም ቀላል ክሶች የእስር ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡