loading
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ማካሄድ ጀመረ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2014 የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጣሂር መሐመድ ያለፉት ጊዜያት የፓርቲው እንቅስቃሴ እንደሚዳሰስና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችም እንደሚቀመጡ አስታውቀዋል። የማዕከላዊ ኮሚቴው ስብሰባ በወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታ አብን ለሕዝቡ ሊያበረክት ስለሚችለው አስተዋጽኦ፣ በቅርቡ በሚደረገው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባዔ ቅድመ ዝግጅት ላይ፣ ስድስተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ምን ይመስል እንደነበርና በሂደቱ የአብን ሚና ምን እንደነበር በስፋት ተነስቶ ጥልቅ ውይይት ይደረግበታል ብለዋል።


አቶ ጣሂር እንዳሉት በሀገሪቱ የተፈጠረውን ጦርነት በመቀልበስ ሂደቱ የአብን ድርሻ እንዴት እንደነበር በስፋት ይፈተሻል፤ የሕልውና ዘመቻው የተመራበት ሀገራዊ ሁኔታን በመገምገም ቀጣይ ሊከናወኑ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይም ይመክራል። ሁሉን አቀፍና አካታች ሀገራዊ መግባባትን በተመለከተ ፓርቲው በተለይ የአማራ ሕዝብን ተጠቃሚ ማድረግ የሚችልባቸውን ጉዳዮችም ይዳስሳል ብለዋል። ማዕከላዊ ኮሚቴው የድርጅቱን የቀጣይ አምስት ዓመታት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቶ
እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።ለሁለት ቀናት በሚቆየው ውይይት ሀገራዊና ወቅታዊ ሁኔታ በስፋት የሚተነተን ሲሆን የድርጅቱን የአሠራር ሥርዓቶች በመከተል በኩል መስተካከል ያሉባቸውን ክፍተቶች በሚመለከትም እንደሚመክር አሚኮ ዘግቧል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *