loading
የአውሮፓ ፓርላማ የሳውዲ ሴቶች ከወንዶች ጥበቃ እንዲላቀቁ አሳሰበ፡፡

የአውሮፓ ፓርላማ የሳውዲ ሴቶች ከወንዶች ጥበቃ እንዲላቀቁ አሳሰበ፡፡

ህብረቱ ሳውዲ አረቢያ ሴቶች ራቸውን ችለው የመወሰን መብታቸውን እንዲጠቀሙ የሚያስችል ህግ ማውጣት እንዳለባት ጠይቋል፡፡

ከአሁን ቀደም በሳወዲ አረቢያ ሴቶች ያለ ወንዶች ጥበቃ በየትኛውም የስራ ዘርፍ እንዲሰማሩ የሀገሪቱ ህግ አይፈቅድም ነበር፡፡

ፓርላማው ሪያድ ይህን ህግ እንድታሻሽል እና ጋብቻንም ሆነ ሌሎች ጉዳዮችን ከወንዶች ጫና ነፃ ሆነው ሴቶች በራሳቸው ምርጫ እንዲወስኑ መፍቀድ ይገባታል ብሏል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው የሳውዲ ሴቶች ድንበር አቋርጠው በሚጓዙበት ወቅት የት እንዳሉ የሚያመላክት የኮምፒውተር መተግበሪያ መዘጋጀቱ እንዳሳሰበውም ህብረቱ ገልጿል፡፡

የሪያድ መንግስት ካለፈው ዓመት ጀምሮ ሲቶች ያለ ወንዶች ጥበቃ እና ክትትል የፈለጉትን እንዲያደረጉ ፈቅዷል ቢባልም አሁንም ድርጊቱ ሙሉ በሙሉ አልቀረም ነው የተባለው፡፡

በሀገሪቱ ሴቶች መኪና  እንዳያሽከረክሩ ማገድን ጨምሮ ሌሎች ህጎች እንዲቀየሩ ሲታገሉ የነበሩ  እና ሳውዲ ያሰረቻቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንዲፈቱም የአውሮፓ ህብረት ጠይቋል፡፡

በአውሮፓ ህብረት የቀረበው ሀሳብ አስገዳጅ ባይሆንም ሳውዲ አረቢያ በጉዳዩ ዙሪያ እንድታስብበት ጫና ያሳድራል ተብሏል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *