loading
የአዲሲቷን ኢትዮጵያ ራዕይ እውን ለማድረግ ሴቶች ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው ተገለጸ

የአዲሲቷን ኢትዮጵያ ራዕይ እውን ለማድረግ ሴቶች ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው ተገለጸ

አርትስ 27/02/2011

 

ይህ የተገለፀው የሴቶች ሃገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ በተካሄደበትና የጀግኒት ለሰላም ንቅናቄ ፕሮግራም በተበሰረበት ወቅት ነው።

በኮንፈረንሱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢዴፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የዳበረ የእርቅ ባህል ያላት  ሀገር በመሆኗ ሴቶች የአዲሲቷን ኢትዮጵያ ራዕይ እውን ለማድረግ  ጉልህ ድርሻ አላቸው።

ሴቶች በሃላፊነት ወንበር ላይ ሲቀመጡ በስልጣን መደላደል የለበትም ያሉት ፕሬዚዳንቷ ለዚህ ደረጃ ያልበቁ ሴቶች የእድገት መሰላሉን እንዲወጡ መርዳትና ማዘጋጀት ነው የሚገባቸው ብለዋል ።

የሴቶች እና የህፃናትን የአደጋ ተጋላጭነት  ለመቀነስ  በዋናነትም ሴቶችን ለማብቃት  በርትተን መስራት ይጠበቅብናልም ነው ያሉት።

በተጨማሪም ጀግኒት የሰላም ንቅናቄ የኢትዮጵያ ሴቶች  ለሀገር ልማት እያበረከቱት ያለውን  አስተዋፆ  ለሁሉም ለማሳወቅና የሰላምን ፋይዳ  በተለይም የሴቶችን አስተዋፆ ለማጉላት አላማ የሰነቀ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ እንደተናገሩት ሴቶች ሰላምን ለማምጣት ታላቅ ሚና አላቸው። በዚህም አስታራቂ  የሆኑ ሴቶችን ማብቃት  እና ማሰልጠን  መቻል አለብን ብለዋል።

የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው በጀግኒት ለሰላም ንቅናቄ ሴቶች ሰላምን ለማስከበር ግንባር ቀደም ድርሻ እንዳላቸውም አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *