የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ለአቅመ ደካሞችና ለጎዳና ተዳዳሪዎች ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ለአቅመ ደካሞችና ለጎዳና ተዳዳሪዎች ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
ቢሮው ለአንድ ሳምንት በሚቆየው ነፃ የምርመራ እና የህክምና አገልግሎት 17 ሺህ ያህል የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በመገኘት አገልግሎቱን ባስጀመሩበት ወቅት ህብረተሰቡ በተለያዩ የጤና ተቋማት የምርመራና ሌሎች የህክምና አገልግሎቶችን እንደሚያገኙ ተናግረዋል። በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች የህክምና ባለሙያዎች እና ነዋሪዎች
ተገኝተዋል።
የጤና ሚኒስቴር ከነሐሴ 16 እስከ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ “በጎነት ለጤናችን” በሚል መሪ ቃል 100 ሺህ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የጤና ምርመራና የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እንደተዘጋጀ መግለፁ ይታወቃል።