የአፍሪካ መሪዎች በህብረቱ ሪፎርም ዙሪያ ሊመክሩ ነው
አርትስ 06/03/2011
መሪዎቹ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ተሰባስበው የአፍሪካ ህብረት የአሰራር ለውጥ ማድረግ አለበት በሚለው ሀሳብ ላይ ይወያያሉ ተብሏል፡፡
ደይሊ ኔሽን እንደዘገበው ህብረቱ ጥርስ የሌለው አንበሳ እየተባለ የሚታማበትን ድክመቱን አርሞና ጠንካራ አሰራሮችን ዘርግቶ ለአህጉሪቱ ጥቅም እንዲተጋ በተደጋጋሚ ሀሳቦች ሲቀርቡ ቆየይተዋል፡፡
በተለይ የአሁኑ የመሪወቹ ጉባኤ የለውጡ ግንባር ቀደም አራማጅ በሆኑት ፓል ካጋሜ ግፊት የሚካሄድ ሲሆን ስብሰባው በመጭው ቅዳሜና እሁድ አዲስ አበባ ላይ ይከናወናል፡፡
በዓለም አቀፍ ቀውሶች የአፍሪካ ሞጋች ቡድን ተቋም ሀላፊ ሆኑት ኢሊዛ ጆብሰን ካጋሜ የሁለት ዓመት የሊቀመንበርነት ጊዜያቸው ከመጠናቀቁ በፊት የመጨረሻ ዘመቻቸውን እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡
በአንፃሩ በሚቀጥለው ዓመት የሊቀመንበርነቱን ቦታ ከሩዋንዳ የምትረከበው ግብፅ በለውጥ አሰራሩ ላይ ብዙም ፍላጎት አላሳየችም ተብሏል፡፡