የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢ- ኮሜርስ ግብይት 2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ሽያጭ ማከናወኑን አስታወቀ፡፡
አዲስ አበባ፣ሐምሌ16፣ 2012 የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢ- ኮሜርስ ግብይት 2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ሽያጭ ማከናወኑን አስታወቀ፡፡ ኮሮናቫይረስ መከሰቱም ለአየር መንገዱ ኪሳራ ቢያስክትልም በቴክኖሎጂ ዘርፍ ግን አዲስ ምዕራፍ እንዲከፍት እንዳስቻለዉ ገልጿል፡፡ የአየርመንገዱ የኢንትግሬትድና ኮሚኒዩኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር አቶ ምረትአብ ተክላይ ለአርትስ እንደተናገሩት ፤በአቪየሽን ኢንዱስትሪ በዉደድሩ ለማለፍ እና ለማሸነፍ ቴክኖሎጂ ትልቁ ምሶሶ በመሆኑ አየር መንገዱ በዘርፉ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አየር መንገዱ አገልግሎቱን በዘመናዊ መንገድ ለደንበኞቹ ለማድረስና በተለይ ወቅቱ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተስፋፋበት በመሆኑ ደንበኞችን ከስጋት ለመታደግ ቴክኖሎጂ ያገዘዉ ሲሆን ፤ በቴክኖሎጂ የሚያካሄዳቸዉ ሽያጮችም ከ4 በመቶ ወደ 40 በመቶ ማደግ መቻሉንም ገልጿል፡፡ ለአየር መንገዱም የኢ-ኮምርስ አገልግሎት በመጠቀሙ ወጪን የቀነሰለት ሲሆን፤ወደፊትም አዳዲስ አሰራሮችን በማስተዋወቅም ደንበኞቹን ለማስደሰት እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡