የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተቀማጭነታቸውን በአማራ ክልል እና ትግራይ ክልል ያደረጉ ቡድኖች በቀጣይ የሊግ ጨዋታዎቻቸውን ያደርጋሉ አለ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተቀማጭነታቸውን በአማራ ክልል እና ትግራይ ክልል ያደረጉ ቡድኖች በቀጣይ የሊግ ጨዋታዎቻቸውን ያደርጋሉ አለ
ከዓታመት በላይ የዘለቀው የሁለቱ ክልል ክለቦች ኩርፊያ ወደ እርቅ የተለወጠ ይመስላል፤ ከወር በፊት በጉዳዩ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጣልቃ በመግባት ከስፖርት ኮሚሽንና የፌዴሬሽን አመራሮች ጋር በመሆን ችግሩን መፍታት በሚቻልባቸው ሁኔታ ዙሪያ ከሁለቱም የክልል አስተዳዳሪዎች ጋር መነጋገር ችለዋል፤ ከሳምንታት በፊት ደግሞ የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል የአማራ ክልል ክለቦች ወደ ትግራይ ቢመጡ በሰላም እናስተናግዳቸዋለን ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ይህንን ተከትሎም አማራ ክልል በኮሚኒኬሽን ቢሮው በኩል ያለውን ዝግጁነት ያሳየ ሲሆን ፋሲል ከነማም ቢሆን በሜዳውና ከሜዳው ውጭ የሚደረጉ ጨዋታዎችን ለማድረግ ፍቃደኛ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፤ ክለቦቹ ለደጋፊዎችና በየደረጃው ለሚገኙ የስፖርት ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ በመስጠታቸው በቀጣይ የሚደረጉ የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ያከናውናሉ ብሏል፡፡