loading
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች ዛሬን ጨምሮ በመጪው ቀናት ይካሄዳሉ::

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች ዛሬን ጨምሮ በመጪው ቀናት ይካሄዳሉ

 

 

የ2011 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ግጥሚያዎች ቢጠናቀቅም ተስተካካይ ጨዋታዎች ይቀራሉ፡፡

 

 

 

ዛሬ ክልል ላይ አንድ ግጥሚያ የሚከናወን ሲሆን ጅማ አባ ጅፋር ጅማ ላይ ደደቢትን 9፡00 ሲል ያስተናግዳል፡፡

 

 

ነገ ሁለት ግጥሚዎች ይደረጋሉ፤ ወደ መቐለ ያቀናው ባህር ዳር ከነማ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር በትግራይ ስታዲየም ይጫወታል፡፡ ሁለቱም ቡኖች በጥሩ ብቃት ላይ መገኘታቸው ግጥሚያውን ተጠባቂ ያደርገዋል፡፡ ጨዋታው 9፡00 ሲል ይካሄዳል፡፡

 

 

በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚመራው መከላከያ ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲም 10፡00 ላይ የምስራቁን ደሬዳዋ ከነማ ይገጥማል፡፡

 

 

ሊጉን በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚሰለጥነው መቐለ በ29 ነጥብ ሲመራ፤ ሲዳመ በ27 ይከተላል፣ ቅዱስ ጊርጊስ በ26 ነጥብ ሶስተኛ ሲሆን ሀዋሳ እና ፋሲል ከነማ በእኩል 24 ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበላልጠው አራተኛና አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

 

ደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረ እና ደደቢት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ፡፡

 

የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት በ11 ጎሎች ይመራል፤ አማኑኤል ገብረሚካኤል ከመቐለ በ10 ይከተላል::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *