loading
የኦሮሞና የጋምቤላ ሕዝቦች የወንድማማችነትና የአንድነት መድረክ እየተካሄደ ነው

የኦሮሞና የጋምቤላ ሕዝቦች የወንድማማችነትና የአንድነት መድረክ እየተካሄደ ነው

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨመሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ተሳታፊዎች በውይይት መድረኩ ለመሳተፍ ትናንት ማምሻውን ጋምቤላ ከተማ ገብተዋል፡፡

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደሬሳ ተረፈ ለፋና እንደተናገሩት  መድረኩ የሁለቱን ክልል ሕዝቦች ለዘመናት ያላቸውን ሰላማዊ ጉርብትና እና ወንድማማችነትን የበለጠ ለማጠናከር ያግዛል።

በሁለቱ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎችም ሆነ ከክልላቸው ውጭ በኦሮሚያና ጋምቤላ የሚኖሩ የሁለቱ ክልል ሕዝቦች ያላቸው በሰላም አብሮ የመኖር እሴት ለሌሎች አካባቢዎችም አርአያ መሆኑን ምክትል ኃላፊው ጠቅሰዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ሁለቱ ሕዝቦች በእኩልነት ላይ የተመሰረተና የሕዝቦች ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሰፈነባትን ሀገር ለመገንባት የታገሉና እየታገሉ ያሉ ሕዝቦች መሆናቸውንም አንስተዋል።

የውይይት መድረኩ ቀድሞ የነበረውን ወንድማማችነትና አንድነት በማጠናከር የሁለቱን ሕዝቦች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር በማጎልበት የጋራ የልማት ተጠቃሚነትን በተሻለ ደረጃ ለማረጋገጥ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያስችላል ሲሉ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደሬሳ ተረፈ ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *