loading
የካቶሊክ  ቤተ ክርስቲያን የኮንጎን የምርጫ ውጤት እየሞገተች ነው

የካቶሊክ  ቤተ ክርስቲያን የኮንጎን የምርጫ ውጤት እየሞገተች ነው፡፡

የኮንጎን የምርጫ ሂደት ከታዘቡት ተቋማት መካከል በሀገሪቱ ትልቅ ተሰሚነት ያላት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አንዷ ናት፡፡

ይሁን እንጂ ቤተ ክርስቲያኗ የምርጫው ውጤት ሲገለፅ አሸናፊው እና እርሷ የታዘበቸው እውነታ እንዳልተገጣጠመላት በይፋ ተናግራለች፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የአፍሪካ ህብረት እና የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ ታዛቢዎችም የቤተ ክርስቲያኗን ሀሳብ ይጋራሉ፡፡

ነገር ግን የስልጣን ሽግግሩን ሰላማዊ ለማድረግ ህዝቡ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሆደ ሰፊ እንዲኑ ከመምክር የዘለለ መግለጫ ከመስጠት ተቆጥበዋል ነው የተባለው፡፡

ተቋማቱ ይህን ያደረጉት በሀገሪቱ ብጥብጥ እንዳይነሳ በመስጋት ሲሆን አንደንድ ዲፕሎማቶች ሌላኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ ማርቲን ፋዩሉ በቀላሉ ማሸነፋቸውን ውስጥ ውስጡን እየተናገሩ ነው፡፡

ፋዩሉ በበኩላቸው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ በምርጫ ኮሚሽኑ አሸናፊ ከተባሉት ፊሊክስ ሽሴኪዲ ጋር ተሻርከው ሀገሪቱን ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ለመምራት የጎነጎት ሴራ ነው ብለዋል፡፡

ይህን ጥርጣሬ ያጎላው ደግሞ የምርጫው ውጤት በፊት ሁለቱ ወገኞች ስልጣን ለመጋራት በድብቅ ድርድር ያደርጉ ነበር የሚል ወሬ መሰማቱ ነው፡፡

ቤልጂየም እና ፈረንሳይም የምርጫ ውጤቱ እንዳስነገጣቸው እና ማብራሪያ የመጠየቅ ሀሳብ እንዳላቸው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው አማካይነት ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *