የዘንድሮውን የአድዋ በዓል በተለየ ሁኔታ ለማክበር ኮሚቴ ተቋቋመ
የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ለአርትስ እንደተናገሩት ፡በአሉን በተለየ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት መደረጉንና ሙሉ የዝግጅቱ መረሀግብርን በተመለከተ በቀጣይ መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
የአድዋ ድል የኢትዮጵያውያን ፅናት የታየበት ታላቅ ድል መሆኑን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከትላት በስቲያ በተጠናቀቀው የአመራር ግምገማ ላይ ተናግረዋል፡፡
በመድረኩም አድዋን አስመልክቶ እንደተናገሩት አዲሱ ትውልድ ታሪኩን ማስታወስ አለበት ያሉ ሲሆን የአድዋ ድል በአል የፓን አፍሪካኒዝም እና የኢትዮጵያውያን ፅናት የታየበት ታላቅ ድልነው በማለትም ገልፀውታል፡፡ ከአዲስ አበባ በላይ የአድዋን ድል የሚያከብር ሊኖር አይችልም ያሉ ሲሆን አባቶቻችን በዛን ወቅት እጅግ ዘመናዊ መሳርያ የታጠቀን ሰራዊት ከአዲስ አበባ ለመግጠም ሲነሱ ያን ጊዜ ነው ያሸነፉት ማለታቸዉ ይታወሳል፡፡