የየመን ሁቲ አማፂያን ተኩስ ለማቆም ዝግጁ ነን አሉ
የየመን ሁቲ አማፂያን ተኩስ ለማቆም ዝግጁ ነን አሉ
አርትስ 10/03/2011
የሁቲ ሚሊሻዎቹ የሳውዲ መራሹ ጦር ሰላምን የሚሻ ከሆነና ወደ ድርድር ከመጣ በኛ በኩል ተኩስ ለማቆም ዝግጁዎች ነን ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በየመን ያለውን ቀውስ ለማስቆም በተፋላሚ ሀይሎቹ ላይ ዓለም አቀፉ ግፊት ቢቀጥልም በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ ብዙ ለውጥ አይታይበትም፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ከሁቲዎቹ በኩል ይሄ ዜና የተሰማው የሳውዲ መራሹ ጦር በየመኗ ሁዴይዳ የወደብ ከተማ የሚያደርገው ጥቃት እንዲቆም ትእዛዝ መስጠቱን ተከትሎ ነው፡፡
የሁቲ አማጺያንም በበኩላቸው በሳውዲ አረቢያ ላይ የሚፈፅሙትን የሰው አልባ አውሮፕላን እና የሚሳኤል ጥቃት እናቆማለን ብለዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የየመን ልዩ ልኡክ ማርቲን ግሪፊዝትስ አዲሱ ዓመት ሳይገባ በተዋጊ ሀይሎቹ መካከል የሰላም ውይይት እንዲደረግ ጥረት እየየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በየመን በሚካሄደው የእርስበርስ ጦርነት ሳቢያ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ሲገደሉ በሀገሪቱ አደገኛ ረሀብ እንዲከሰትና በርካቶች በስቃይ ኑሯቸውን እንዲገፉ ተገደዋል፡፡