loading
የጆሴፍ ካቢላ ፓርቲ የኮንጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ሊመርጥ ነው፡፡

የጆሴፍ ካቢላ ፓርቲ የኮንጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ሊመርጥ ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ሺሴኬዲ ፓርቲያቸው ኮመን ፍሮንት ፎር ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሰየም የሚያስችል ድምፅ ባለማግኘቱ የጥምር መንግስት ለመመስረት ተገደዋል፡፡

በቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዝዳት ጆሴፍ ካቢላ የሚመራው ፒፕልስ ፓርቲ ፎር ዲሞክራሲ  አብላጫውን የፓርላማ መቀመጫ በማሸነፉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን  የመሾም ስልጣን አግኝቷል፡፡

የካቢላ ፓርቲ ካሉት 485 የፓርላማ መቀመጫዎች 342 ድምፅ  በማግኘት ነው ስልጣኑን የተጋራው፡፡

ካቢላ ምንም እንኳ የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ በፈቃዳቸው ቢለቁም አሁንም በኮንጎ ፖለቲካ ውስጥ በተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው ቀጥለዋል የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡

እንደ ማርቲን ፋዩሉ ያሉ በምርጫው እጩ ሆነው የቀረቡ ተቀናቃኞች ገና በቅስቀሳው ወቅት ይህ እንደሚሆን ተናግረው ነበር፡፡

በወቅቱ ካቢላ ስልጣን በቃኝ ሲሉ ሺሲኬዲን እንዲመረጡ በማድረግ በቀጣዩ አስተዳደር ውስጥ ቁልፍ ቦታ እንዲኖራቸው ሲያመቻቹ ነው የሚል ትችት ተነስቶባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *