የጦር መሳርያ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙት የ81 ዓመቱ አዛውንት በፅኑ እስራት ተቀጡ።
የጦር መሳርያ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙት የ81 ዓመቱ አዛውንት በፅኑ እስራት ተቀጡ።
አቶ አለማየሁ ቦኩ ሆርዶፋ የተባሉ የ81 ዓመት እድሜ ያላቸዉ ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀፅ 481 (ሀ) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ፍቃድ ሳይኖራቸው ወይም ሕግን ተቃራኒ በሆነ መንገድ መጋቢት 07/2011 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው አጣና ተራ እፎይታ አካባቢ በአጠቃላይ 1022 ብር( አንድ ሺህ ሃያ ሁለት ብር) የሚገመቱ የተለያዩ የጦር መሳርያ ጥይቶችን ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ በመሆኑ በፈፀሙት የጦር መሳርያ መነገድ ወንጀል በአቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባቸዋል ።
ከሳሽ ዐቃቤ ህግም ለፌደራሉ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ወንጀል ችሎት የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር የሰው ፣ የሰነድና የኢግዚቪት ማስረጃዎች በማቅረቡና በማስረዳቱ ተከሳሽ ክሱን ማስተባበል ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት ግንቦት 13/2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተከሳሽ ላይ የየቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።
የእስራት እርከኑን በእርከን 10 ስር በመያዝ ተከሳሹ ከዚህ ቀደም የነበራቸው መልካም ባህሪ ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪና በእርጅና ምክንያ የአይን ታማሚ መሆናቸው ሶስት ማቅለያ ተይዞላቸው በእስራት እርከን 7 ፍቃደ ስልጣን ተከሳሹ በ1 ዓመት ፅኑ እስራት አንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል ።
ምንጭ ፤- የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ