loading
የፊቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው

የፊቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው

የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው።

ዛሬና  የጀመረዉ የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።

የፊቼ ጫምባላላ በዓል እየተከበረ የሚገኘውም በዓሉን በሚያንፀባርቁ የተለያዩ ባህላዊ  ስነስረዓቶች ነው።

ዛሬ በሀዋሳ በሚከናወነው የፊቼ ጫምባላላ በዓል ስነ ስርዓት ላይ የሲዳማ ብሄር ባህልና ቋንቋ የተመለከተ ሲምፖዚዬም ይካሄዳል።

የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምባላላ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አለም አቀፍ  ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወቅ ነው።

በዓሉ ነገም ተከብሮ ይዉላል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *