የፖለቲካ ቀውስ እና የኩቪድ 19 ወረርሽኝ ቦልሶናሮን አስጨንቋቸዋል ተባለ::
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2013 የፖለቲካ ቀውስ እና የኩቪድ 19 ወረርሽኝ ቦልሶናሮን አስጨንቋቸዋል ተባለ:: የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጃየር ቦልሶናሮ ከዚህ ቀደም ብራዚላውያን ስለ ኮቪድ -19 ማልቀስ ማቆም እንዳለባቸው ሲናገሩ ነበር ጃየር ቦልሶናሮ የጦር ኃይሎች ፣ የባህር ኃይል እና የአየር ኃይል ሀላፊዎች በሙሉ ቸል ባሉበት በዚህ ወቅት አገሪቱ በየቀኑ ከፍተኛ የኮቪድ -19 የሞት ቁጥር እያስመዘገበች ትገኛለች ሲል ቢቢሲ በዘገባዉ አስነብቧል፡፡
ቦልሶናሮ በጦር ኃይሉ ላይ ተገቢ ያልሆነ ቁጥጥር ለማድረግ ባደረጉት ሙከራና ከስልጣን የማንሳት ተግባር የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጎባቸዋል፡፡
ሚስተር ቦልሶናሮ ለኮቪድ -19 በሰጡት ያልተገባ ምላሽ ተቀባይነታቸዉ እጅጉን ቀንሷል፡፡ በብራዚል ወደ 314,000 የሚጠጉ ሰዎች የሞቱ ሲሆን ማክሰኞ እለት በቀን 3,780 ሞተዋል፡፡ ቦልሶናሮ ወረርሽኙ ከሰጡት ግምት በላይ በማየሉ ቀዉስ እያደረሰ በመሆኑ ትልቁ ቀውስ ገጥሟቸዋል ተብሏል፡፡
በሃገሪቱ ከ12.5 ሚሊዮን በላይ በኮቪድ 19 መያዛቸዉ የተረጋገጡ ሰዎች መኖራቸዉ ታዉቋ፡፡ ከሁለት አመት በፊት ወደ ስልጣን የመጡት የብራዚሉ ፕሬዝዳንት የኳራንቲን እርምጃዎችን በተከታታይ በመቃወም በኢኮኖሚው ላይ የሚደርሰው ጉዳት በራሱ የኮሮና ቫይረስ ከሚያስከትለው ውጤት የከፋ
እንደሚሆን ይናራሉ ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና የመከላከያ ሚኒስትሮቻቸው ሥራቸውን ከለቀቁ በኋላ ሰኞ ዕለት ፕሬዚዳንቱ የካቢኔያቸውን ሹመት እንዲያስተካክሉ ተገደዋል ፡፡