loading
ግብፅ  በቀይ ባህር የዓሳ ማጥመድ ስራ እንዳይካሄድ ከለከለለች

ግብፅ  በቀይ ባህር የዓሳ ማጥመድ ስራ እንዳይካሄድ ከለከለለች

የፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ መንግስት ይህን እርምጃ የወሰደው በአካባቢው ስነ ህይዎታዊ ሚዛንን ለመጠበቅ በማሰብ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

የዓሳ ሀብት ልማት ባለስልጣን መስሪያ ቤትን በሀላፊነት የሚመሩት ዶክተር አይመን አማር እንዳሉት በፈረንጆቹ ከየካቲት እስከ መስከረም ለሰባት ወራ ያህል በቀይ ባሀር አካባቢ ዓሳ ማስገር አይቻልም፡፡

የግብፁ አክባር አል ዮም ጋዜጣ እንደዘገበው የሀገሪቱ መንግስት የወሰደው እርምጃ የውሀ ውስጥ ብዛሃ ህይዎት እንዳይጎዳ ያደርጋል፡፡

በየዓመቱ ከቀይ ባህር የሚሰበሰበው 60 ሺህ ቶን የዓሣ ምርት የግብፅን የዓሣ ፍላጎት የሚያሟላው ሶስት በመቶውን ብቻ መሆኑን ባለ ስልጣናቱ ተናግረዋል፡፡

በዚህም  የተነሳ ግብፅ የዜጎቿን ከፍተኛ የዓሣ ፍላጎት ለማሟላት ስትለ በየዓመቱ ከውጭ ሀገር 300 ሺህ ቶን የዓሳ ምርት ታስገባለች፡፡

ባለፈው ዓመት በመንግስት ድጋፍ የተደረገለት ዓሰሣ እርባታ ዘርፍ ምርቱ አንዲጨምር ማድረጉ እጥረቱን ለመሸፈን እገዛ ማድረጉም ተመልክቷል፡፡

አሁን የተወሰደው ዓሣ ማስገርን የሚከለክል እርምጃ የዓሣ ዋጋ እንዲጨም ያደርጋል የሚል ስጋት ቢፈጥርም  ባለ ስልጣናቱ ግን ችግር እንደማይኖር ለህዝቡ ማረጋገጫ ሰጥተዋል ነው የተባለው፡

በመንገሻ አለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *