ግብፅ ጄኔራል ከሊፋ ሀፍታርን እየደገፈች ነው፡፡
ግብፅ ጄኔራል ከሊፋ ሀፍታርን እየደገፈች ነው፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ያለውን የትሪፖሊን መንግስት ለመጣል ነፍጥ ያነሱት ጄኔራል ከሊፋ ሀፍታር ከፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ መንግስት የተላከላቸውን የጦር መሳሪያ በእጃቸው አስገብተዋል ተብሏል፡፡
አል አረቢያ አል ጀዲድ እንደዘገበው ግብፅ ቀላል የነፍስ ወከፍ ጦር መሳሪያዎችን፣ ምግብ እና አልሳባትን ነው ለሀፍታር ወታደሮች የላከችው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የግብፅ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ካይሮ ከአቡዳቢ፣ከፓሪስ፣ ከሪያድ እና ከሞስኮ ጋር በሊቢያ ሰላም እንዲሰፍን በሰፊው መክራለች ብሏል፡፡
ሀፍታር ከአሜሪካም ድጋፍ እንዳላቸው የሚነገር ሲሆን አልሲሲ ዋይት ሀውስን በጎበኙበት ወቅት ይህንኑ ጉዳይ ለትራምፕ እንደነገሯቸውም ዘገባው ያትታል፡፡
መንገሻ ዓለሙ