ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከቢል ጌትስ ጋር ተወያይተዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከቢል ጌትስ ጋር ተወያይተዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዳቮስ የዓለም ኢኮኖሚ ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ አካላት ጋር ተወያይተዋል።
በዚህም ከቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ተባባሪ ሊቀመንበር ከሆኑት ቢል ጌትስ ጋር ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን ፋውንዴሽኑ በኢትዮጵያ በጤና፣ በግብርና፣ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ዘርፎች ላይ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩና ቢል ጌትስ በግብርና መስኖና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ለመተባበር ተስማምተዋል::
በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአሊባባ ሊቀመንበር ጃክ ማ ጋር ተገናኝተው ገንቢ ውይይት አድርገዋል። ሁለቱ ወገኖች ምጡቅ የቴክኖሎጂ እድገት በገበያ እና ማህበረሰብ ላይ የሚያመጡትን ለውጥ በተመለከተ ተወያይተዋል ተብሏል።
ጃክ ማ በኢትዮጵያ ውስጥ የህዝቦችን የዕለት ተዕለት ህይወት በሚጠቅም መልኩ የቴክኖሎጂ ከተማዎች ልማት መስክ ሀብት ለማፍስስ ያሉ አማራጮችን ለመለየት ተስማምተዋልም ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሲውዘርላንድ ዳቮስ የነበራቸውን የአውሮፓ ቆይታ በተሳካ ሁኔታ አጠናቀዉ ወደ ቤልጅየም ብራስልስ ማቅናታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃውን አድርሶናል::