ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሁን በስዊዘርላንድ ዳቮስ ይገኛሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሁን በስዊዘርላንድ ዳቮስ ይገኛሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስዊዘርላንድ ዳቮስ በሚካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ነው ወደ ስፍራው ያቀኑት።
በፎረሙ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዓለም ሃገራት መሪዎች በተገኙበት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከጠቅላይ ሚኒስተር ጽ/ቤት እንዳገኘነዉ መረጃ የዶክተር አብይ ንግግር በኢትዮጵያ ባለፉት 10 ወራት ስለተደረጉ ማሻሻያዎችና ለውጦች ላይ ያተኩራል፡፡
የስዊዘርላንዷ ዳቮስ ከተማ የኢኮኖሚ ጉባኤ የተለያዩ ሃገራት እና የቢዝነስ መሪዎች በየአመቱ በመገናኘት በወደፊቱ የዓለም ኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ ሚመክሩበት ነዉ።