loading
ጠ/ሚር አብይ አሕመድ የጊዴቦ ግድብ ስራ ፕሮጀክትን ዛሬ መረቁ::

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የጊዴቦ ግድብ ስራ ፕሮጀክትን ዛሬ ጥር 26 ቀን 2011 መረቁ:: በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች የሚገኘው ይህ ግድብ 25.8 ሜትር ከፍታና 335 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ከ62.5 ሚሊዮን ኪዩብ በላይ ውሃ የመያዝ አቅም አለው::

ግድቡን ሰርቶ ለማጠናቀቅም ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ፈጅቷል:: በዛሬው ምረቃ ስነስርዓት ላይም የኦሮምያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ለማ መገርሳና የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሚሊዮን ማቲዎስ ተገኝተዋል::

ምንጭ ፦ጠ/ሚር ጽ/ቤት

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *