loading
ፈረሰኞቹ አዲስ ብሪታኒያዊ አሰልጣኝ ቀጠሩ

አርትስ ስፖርት 29/02/2011

ቅዱስ ጊዮርጊስ ቫዝ ፒንቶን ካሰናበተበኋላ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ገበያ ላይ ወጥቶ የነበረ ሲሆን አሁንከብሪታኒያዊው የ62 ዓመት አሰልጣኝ ስቴዋርት ጆን ሀል ተስማምቷል፡፡ አሰልጣኝ ስቴዋርት ጆን ሀል የዩኤፋየአሰልጣኛነትና የአሰልጣኞች አሰልጣኝነት ላይሰንስ ያላቸው ናቸው ተብሏል። አሰልጣኙ በቀደመው ጊዜየበርሚንግሃም ሲቲ እግር ኳስ አካዳሚ ዳይሬክተር እና የተተኪ ቡድኑ እና ከ18 ዓመት በታች ቡድኑ አሰልጣኝ የነበሩሲሆን በርሚግንሐምን ለቀው የህንዱን ፑኔ ሲቲን ከ2007-09 እ.ኤ.አ አሰልጥነዋል፡፡ በ2009 መጨረሻ ሴንትቪንሰንት እና ግሬናዲያንስ ዋናውን እና ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት በመያዝ ከ20 ዓመትበታች ቡድኑን በኮንካካፍ ማጣሪያ ቡድኑን ከምድቡ አንደኛ በማድረግ ማሰለፍ ችለዋል፡፡ በ2010 እ.ኤ.አየዘንዚባር ብሄራዊ ቡድን አለቃ ሆነው ተሹመዋል፡፡ ከዚያም የታንዛኒያውን አዛምን በመያዝ ቡድኑን በቮዳኮምፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሆኖ እንዲያጠናቅቅና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የማፓንዱዚ ዋንጫን እንዲያሸኝፍአድረገዋል፡፡ ከ2 ዓመት ቆይታ በኋላ ከቦርዱ ጋር ባለመስማማታቸው አዛምን ለቀው በ12 መስከረም 2012 እ.ኤ.አ የኬንያውን የተስካር ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለብ ሶፋፓካን ተቀላቅለዋል፡፡ ነገር ግን የሶፋፓካ ቆይታቸው ከ7 ሳምንታት አልዘለለም ተመልሰው አዛምን መያዝ ችለዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2013 ሌላኛውን የታንዛኒያ ክለብ ሲምቢዮንፓውርን፤ ልክ እንደ አንድ የስራ ድርሻ የታንዛኒያን ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖችን አሰልጥነዋል፡፡ በድጋሚወደ አዛም ተመልሰው የሴካፋን የክለቦች ዋንጫ (ካጋሚ ካፕ) ማሸነፍ ችለዋል፡፡ ከአዛም በ2016 ወደ ኬንያውኤ.ሲ ሌዎፓርድ ለ2 ዓመት በሚቆ የውል ስምምነት ቢቀላቀሉም ከ1 ዓመት በላይ መቆት አልቻሉም፡፡ ከ2018 ጀምሮ የባንግላዴሹን ሳይፍ ስፖርቲንግ ክለብ በማሰልጠን ለ18 ተከታታይ ጨዋታዎች ያለሽንፈት መጓዝ ችለዋል፡፡አሁን ደግሞ ፈረሰኞችን ለማሰልጠን ተስማምተዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተቀላቀሉ በኋላ ተከታዩን አስተያየት ለክለቡይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ሰጥተዋል። “በባንግላዴሽ ቆይታዬ ጥሩ ተከፋይ አሰልጣኝ ነበርኩ። በሊጉም ዛሬ እዚህ አስክመጣድረስ በ18 ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ሽንፈትን አላስተናገድኩም፡፡ ነገር ግን ለ8 ዓመታት በምስራቅ አፍሪካ በተለያዩክለብና ብሔራዊ ቡድኖች ስቆይ ቅዱስ ጊዮርጊስን ማሰልጠን እፈልግ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ከክለቡ ጥያቄ ሲቀርብልኝባሳልፈው የምፀፀትበት ውሳኔ ይሆናል ብዬ የልቀቁን ጥያቄ ለክለቤ አቀረብኩኝ እነርሱም መልቀቅ ባይፈልጉምጥያቄን ተቀብለውኛል፡፡ ” ወደ በርካታ ደጋፊዎች ባለቤት ወደሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ መጥቻለሁ በዚህም ደስተኛነኝ”፡፡ አዲሱ የፈረሰኞቹ አለቃ፡፡ በነገው ዕለት ስራ የሚጀምሩ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርትማህበር ስራ አመራር ቦርድ ዋና ፀሀፊ፣ የቡድን መሪ እና ኮቺንግ ስታፍ ጋር ትውውቅ አድርገዋል። ከ1996 ጀምሮበመደበኛነት የውጪ አሰልጣኞችን እየሾመ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ15 ዓመታት ውሰጥ 11ኛ የውጪ ዜጋአሰልጣኙን ቀጥሯል። ምንጭ፡ Saint George S.A

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *