loading
ፊሊክስ ሽሴኪዲ በነገው እለት የኮንጎ ፕሬዝዳንት ለመሆን ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ፡፡

ፊሊክስ ሽሴኪዲ በነገው እለት የኮንጎ ፕሬዝዳንት ለመሆን ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ፡፡

የሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት በውዝግብ በተሞላው የዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ የምርጫ ውጤት የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ምርጫው  እንደተጠናቀቀ ሺሴኪዲ ማሸነፋቸውን የምርጫ ኮሚሺኑ ይፋ ሲያደርግ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ታዛቢዎቸ  ያቀረቡልኝ ሪፖርት እና ውጤቱ ተለያልቷ በሚል ተቃውሞዋን አሰምታለች፡፡

የአፍሪካ ህብረትም ሰሞኑን አዲስ አበባ ላይ በጉዳዩ ዙሪያ መክሮ የምርጫው ጠቅላላ ውጤት ዘግይቶ እንዲገለፅ የሚል ምከረ ሃሳብ አቅርቦ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ የኮንጎ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ሺሴኪዲ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ማገልገል የሚያስችላቸውን ድምፅ አግኝተዋል በማለት ወስኗል፡፡

አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው ፊሊክስ ሺሴኪዲ ኮንጎ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1960 ነፃነቷን ካገኘች ወዲህ  በምርጫ ወደ ስለጣን የመጡ የመጀመሪያው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ናቸው፡፡

በሀሪቱ በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር ሲደረግም ይህ በኮንጎ ታሪክ የመጀመሪያው ነው፡፡

አዲሱ ፕሬዝዳንት የምርጫ ኮሚሺኑ ባስቀመጠው መርሀ ግብር መሰረት በነገው እለት ቃለ መሃላ ፈፅመው ስልጣናቸውን ከጆሴፍ ካቢል ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *