loading
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከህመማቸው አገግመው በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ስራ ይመለሳሉ ተባለ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከህመማቸው አገግመው በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ስራ ይመለሳሉ ተባለ:: በቤተ መንግስታቸው ተወሽበው የከረሙት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኮሮናቫይረስ ማገገማቸውን ሀኪሞቻቸው ተናግረዋል፡፡ በመጀመሪያ በዋይት ሀውስ ቀጥሎም በወታደራዊ ሆስፒታል ህክምናቸውን የተከታተሉት ትራምፕ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ጊዜየን ማጥፋት አልፈልግም የምጫ ክርክሬን በፊት ለፊት ማድረግ እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡

የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ግን የፕሬዚዳንቱን ጤንነትና ስራቸውን በአግባቡ የመወጣት ብቃታቸውን የሚያጣራ ኮሚሽን አቃቁማለሁ ብለዋል፡፡ ፔሎሲ እንዳሉት 25ኛውን የአሜሪካ ህገ መንግስት ማሻሻያን መሰረት አድርጎ ነው ኮሚሽኑ የሚቋቋመው፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ትራምፕ የፔሎሲን መግለጫ ከሰሙ በኋላ ሀሳባቸውን ረብ የለሽ በማለት አጣጥለውታል፡፡ የትራምፕ የግል ሀኪም ለዋይት ሀውስ በፃፉት የውስጥ ማስታወሻ የፕሬዚዳንቱ ጤንነት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ትራምፕ ከወታደራዊ ሆስፒታል ወጥተው ወደ ዋይት ሀውስ በተለሱበት ወቅት ስለ ጤንነታቸው መግለጫ ሲሰጡ የፊት መሸፈኛ ጨጭንብላቸውን አውልቀው በሽታውን አትፍሩት ማለታችው ብዙ ወቀሳ አስከትሎባቸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *