loading
ሀገር በቀል ባህላዊ እሴቶች ለቱሪስቶች መስህብ እንዲሆኑና የሀገር ገጽታን ለመገንባት እንዲያስችሉ በስፋት ማልማት እና ማስተዋወቅ ይገባል ተባለ

ሀገር በቀል ባህላዊ እሴቶች ለቱሪስቶች መስህብ እንዲሆኑና የሀገር ገጽታን ለመገንባት እንዲያስችሉ በስፋት ማልማት እና ማስተዋወቅ ይገባል ተባለ።


10ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ሳምንት ˝ባህል ለህዝቦች ሰላም እና አንድነት˝ በሚል መሪ ቃል በኤግዚቢሽን ማእከል ተከፍቷል፡፡

 

የባህል ሳምንት ኤግዚቢሽኑን በይፋ የከፈቱት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ብዙነሽ መሠረት የባህል ሳምንታት በየደረጃው መከበራቸው እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በርካታ ብሄር ብሄረሰቦችን እርስ በእርስ ለማቀራረብ ያግዛል ብለዋል፡፡

በመሆኑም በእነዚህ ሳምንታት ሀገር በቀል ባህላዊ እሴቶች ቱሪስቶችን በመሳብ እና የሀገር ገጽታን በመገንባት ረገድ የሚኖራቸው ሚና የጎላ በመሆኑ በስፋት ማልማት እና ማስተዋወቅ ይገባል ነው የተባለው፡፡

 

የአዲስ አበባ ባህል ፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ሓላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ እንዳሉት ፌስቲቫሉ በከተማዋ የሚገኙ ባህላዊ እሴቶችን እና ቅርሶችን ከማስተዋወቅ ባለፈ በህዝቦች መካከል መቀራረብን የሚፈጥርና በሰላም አብሮ የመኖር እሴቶች እንዲጎለብቱ የሚያደርግ ነው ፡፡

በዚህ ከተማ አቀፍ የባህል ሳምንት ሀገር በቀል ባህላዊ ምርቶች እና የዕደ ጥበብ ውጤቶች እንዲሁም ኪነ-ጥበባዊ ትዕይንቶች ለእይታ የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

በተለይ መጤ ባህሎችን እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል እንዲሁም ባህላዊ እሴቶችን ለማጎልበት በሚያስችሉ ተግባራት ዙሪያ በምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዉ ወይይት ይደረግባቸዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *