loading
ህብረተሰቡ ሁለተኛውን ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ወደ ክትባት መስጫ ጣቢያዎች በመቅረብ እንዲከተብ ጥሪ ቀረበ

የሁለተኛዉ ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ እድሚያቸው 12 አመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሁሉ በመንግስት ጤና ተቋማትና በጊዚያዊ ክትባት መስጫ ጣቢያዎች ከየካቲት 7 እስከ 16/2014 ዓ.ም መስጠት ተጀምሯል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶር ዮሃንስ ጫላ በሰጡት መግለጫ እንዳሳዎቁት፤
እስካሁን ሰባት ሺህ 426 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በወረርሽኙ ህይወታቸው አልፏል።


ክትባቱን ተደራሽ ከማድረግ አንጻርም፤ እስካሁን አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዬን ሰዎች አንድ ጊዜ፤ 700 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ሁለት ጊዜ ተከትበዋል ብለዋል። ይህ ወቅት የቫይርሱ 4ኛ ዙር ማእበል የተነሳበት በመሆኑ ህብረተሰቡ በመከተብና ሌሎችን በማስከተብ ወረርሽኙን እንዲግታ ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ በሁለተኛው ዙር ዘመቻ ለግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ክትባት ለመስጠት ግብ መቀመጡን በመግልጫው ተጠቅሷል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *