loading
ህገወጥ ነጋዴዎችን በአከባቢያችሁ ለሚገኝ ፖሊስ ጠቁሙ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣2013  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ለንግድ ማህበረሰቡ ማሳሰቢያ ሰጠ፡፡ ቢሮው አንዳንድ ስግብግብ ነጋዴዎች ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ በአቋራጭ ለመክበር እና ሆን ብሎ ህገ-ወጥ የዋጋ ጭምሪ እና ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ለመፍጠር ጥረት ማድረግ ላይ መሆናቸውን ድርሼበታለሁ ብሏል፡፡ ስለሆነም በማንኛውም ንግድ ስራ ላይ ተሰማርታችሁ የምትገኙ ነጋዴዎች ለሽያጭ በሚቀርቡ ማለትም በተለይ ከውጪ ሃገር የገቡ ወይም በሃገር ውስጥ የተመረቱ ማንኛውም ዕቃዎች ፣ የግብርና ምርቶች ፣የምግብ እና መሰል ሸቀጣ ሸቀጦች ፣ ማንኛውም አገልግሎቶች ላይ ዋጋ መጨመር በጥብቅ የተከለከለ ነው ብሏል፡፡

በተጨማሪም ምርት መደበቅ እና ማከማቸት፣ ምርትን ከባዕድ ነገር ጋር መቀላቀል፣ ሚዛና ማዛባት፣ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች ለገበያ ማቅረብ፣ ያለደረሰኝ መገበያየት፣ ከአድራሻ ውጪ መገበያየት እና ሌሎች በህግ የተከለከሉ ድርጊቶችን መፈጸም በንግድ ህግ የሚያስቀጣ በመሆኑ ነጋዴዎች ጥንቃቄ አድርጉ ብሏል፡፡
የከተማችን ነዋሪዎች ይህን ማስጠንቀቂያ ተላልፎ የሚገኙ ህገወጥ ነጋዴዎች በአከባቢው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም በቢሮው ነጻ ስልክ ቁጥር 8588 ወይም 0111-11-55-81 ደውላችሁ አሳዉቁኝ ብሏችኋል፡፡ ወቅቱ ከትርፋችን በላይ አገራችንና ህዝባችን ስለማትረፍ የምናስብበት መሆኑም ሊዘነጋ እንደማይገባ
ቢሮው አሳስቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *