ህገ ወጥ ስደተኞች በተሰረቀ ጀልባ እግሊዝ ሲገቡ ተያዙ
አርትስ 05/03/2011
ስደኞች በዚህ መልኩ ወደ እንግሊዝ ለመግባት ሲሞክሩ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ስደተኞቹ የተጓዙባት 12 ሜትር ርዝመት ያላት የዓሳ ማጥመጃ ጀልባ የተሰረቀችው ከፈረንሳይ መሆኑን ባለስልጣናት ባለንብረቱን ጠይቀው አረጋግጠዋል፡
ጀልባዋ ባልተለመደ መስመር ስትጓዝ ያስተዋሉት የፈረንሳይ ድንበር ጠባቂዎች በፍጥነት ለእንግሊዝ የፀጥታ ሰወች መረጃ በመስጠታቸው ስደተኞቹ እግራቸው መሬት እንደረገጠ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
እነዚ ህገ ወጥ ስደተኞች የየት ሀገር ዜጎች እንደሆኑ እና የጉዟቸው መነሻ ከየት እንደሆነ ገና እየተጣራ ሲሆን የፈረናሳይ ፖሊስ በበኩሉ ስለ ጀልባዋ ምርመራ ጀምሯል፡፡
የፈረንሳይ የድንበር ጠባቂ ፖሊስ ወደ አንግሊዝ በሚያስተላልፈው የውሃ መስመር በ2016 23 ጊዜ በ2017 ደግሞ 12 ጊዜ ስደተኞች ሊያቋርጡ ሲሉ መያዙን ተናግሯል፡፡