loading
ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የቦንድ ሳምንት  በማዘጋጀት 500 ሚሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዷል፡፡

ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የቦንድ ሳምንት  በማዘጋጀት 500 ሚሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዷል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ከመጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በሚኖረው የቦንድ ሳምንት 500 ሚሊዮን ብር ለማግኘት መታቀዱን ገለጸ።

ለግድቡ ግንባታ በሰባት ወራት ጊዜ ውስጥ 400 ሚሊዮን ብር ብቻ መሰብሰቡን ያስታወሰዉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ኃይሉ አብርሃም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ከ8100 A የአጭር የጽሑፍ መልዕክት በተጨማሪ፤ ከመጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የቦንድ ሳምንት ለማካሄድ ታስቧል።

የቦንዱ ሳምንት ከልማትና ከንግድ ባንኮች ጋር በጥምረት በመላው አገሪቱ የሚሄድ ሲሆን በዚህም ጊዜ 500 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታስቧል።

ቀደም ብሎ በነበሩት ዓመታት በተደረጉ የቦንድ ሳምንቶች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ አለመቻሉን የጠቀሱት አቶ ኃይሉ፤ አሁን ላይ ያለውን የሕዝብ ስሜት በመያዝ እቅዱን ለማሳካት እንደሚሰራ አመልክተዋል።

ሌላው የንቅናቄ ሥራውን ይበልጥ ለማጠናከር ሰነድ ተዘጋጅቶ ለውይይት ለማቅረብ ዝግጅት ተደርጓል  የሚሉት አቶ ኃይሉ፤ ሰነዱን ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ውይይት እንደሚያደርግበት ተናግረዋል።

የተዘጋጀው ሰነድ ግድቡ ያለበትን አጠቃላይ ሁኔታ የሚያሳይ ሲሆን የግድቡ ግንባታ መቼ ተጀመረ? ጠቀሜታው፣ ግንባታው የደረሰበት ደረጃ፣ ሕዝባዊ ተሳትፎው ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ፣ የፐብሊክ ዲፕሎማሲና የዳያስፖራ ተሳትፎ፤ እንዲሁም አሁን ያለው የዲፕሎማሲ ሁኔታና ከሕዝቡ ምን እንደሚጠበቅ የሚገልጹ ሀሳቦችን ማካተቱን አስረድተዋል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *