loading
ለሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በሙኒክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በሙኒክ ተካሄደ፡፡ በጀርመን ሙኒክ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ አዘጋጅነት በተዘጋጀው በዚህ ፕሮግራም ላይ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል። በተለያዩ ዘርፎች ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር “ደግሞ ለዓባይ” በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል። በፕሮግራሙ ላይ ኢትዮጵያዊያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ በቦንድ ግዥ፣
በመጽሔት ሽያጭና በስጦታ በከፍተኛ ቁጭትና ፍላጎት የተሳተፉ ሲሆን በዚህም ከ15 ሺህ ዩሮ በላይ ገቢ ማሰባሰብ ተችሏል።

በጀርመን – ፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል ጽህፈት ቤት ቆንስል ጄኔራል አቶ ፈቃዱ በየነ ድጋፉን አስመልክቶባስተላለፉት መልእክት በሚወዷት ሀገራቸው ሥም ተሰብስበው ሕዳሴ ግድቡን ለመደገፍ በመገኘታቸው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። በጀርመን ሙኒክ አካባቢ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሁሉም ዘርፍ ሀገራቸውን ሲደግፉ የነበሩ መሆናቸውን በማስታወስ፤ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቦንድ የተለመደ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉና
በቀጣይነት ይህንን ስብስብ ወደ መላው የኢትዮጵያ ቀን በማሳደግ በአንድነት ከሀገራቸው ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

በጀርመን ሙኒክ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የቦንድ ግዢውን ሲፈጽሙ እንደተናገሩት÷ በዚህ ታሪካዊ ቀንም የዜግነታቸውን ድርሻ ለመወጣት ሀገራቸውን ለመደገፍ በመገኘታቸው የዜግነት ክብር እንደሚሰማቸው በመግለጽ በሁሉም ዘርፍ ድጋፋችንን አጠናክረን በማስቀጠል ለሀገራችን ያለንን ፍቅር በተግባር እንገልጻለን ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *