loading
ለሕገ ወጥ ስደትና ለጎዳና ኑሮ የሚዳረጉ ህጻናትን ለመታደግ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ሚኒስቴሩ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 ለሕገ ወጥ ስደትና ለጎዳና ኑሮ የሚዳረጉ ህጻናትን ለመታደግ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ሚኒስቴሩ አስታወቀ፡፡ የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው በሕገ ወጥ የሕፃናት ዝውውር ላይ ያተኮረ የባለ ድርሻ አካላት ውይይት ተካሄዷል።

በርካታ ሕፃናት በመማሪያ እድሜያቸዉ ለሕገ-ወጥ ስደት የሚዳረጉ ሲሆን በሀገራችን በተለያዩ ከተሞች ሕፃናት ውሎና አዳራቸውን በጎዳናዎች ላይ ያደርጋሉ፤ ከዚህም አልፎ ሴት ሕፃናት ያለዕድሜያቸው ልጆች ወልደው በጎዳና ላይ ህይወታቸውን በከፋ ሁኔታ ይገፋሉ ተብሏል:: በመሆኑም ለዚህ አስከፊ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ያስችል ዘንድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የጋራ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ መድረክ ተዘጋጅቷል” ሲሉ በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሕፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክብርት ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ለጎዳና ኑሮ የተዳረጉ 150 ሺህ የሚደርሱ ሕፃናት አብዛኛውን ጊዜ ለመሰረታዊ አገልግሎቶች ተደራሽ አይሆኑም ተብሏል።
በሌላ መልኩ ለሕገ ወጥ ዝውውር ሰለባ የሆኑ ሕፃናትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር መልሶ የማቀላቀል ስራ ላይ ያሉ ተግዳሮቶች በርካታ በመሆናቸው ችግሩ በመሰረታዊነት ሳይቀረፍ አሁንም ድረስ ሕፃናትን ተጎጂ እያደረግ ቀጥሏል። ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር ውስጥ 52 በመቶ ሕፃናት እንደሆኑና ከነዚህም ውስጥ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑት ወላጆቻቸውን በተለያዩ ምክንያቶች ያጡና ለችግር ተጋላጭ መሆናቸው በቀረቡት የመነሻ ጽሑፎችና ገለጻዎች ላይ ተብራርቷል።

በተጨማሪም ለሕገ ወጥ የሕፃናት ዝውውር ከሚዳረጉ ሕፃናት መካከል 94 በመቶ የሚሆኑት ወንድ ሕፃናት በመሆናቸው ምክንያት ችግሩ በዋናነት ወንድ ሕፃናት ላይ ያተኮረ መሆኑም ተገልጿል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *